አመሰግናለሁ! ከሁለት አመት በፊት በአሩሻ ታንዛኒያ በቴድ መድረክ ቆሜ ነበር ስለምኮራበት የፈጠራ ስራዬ ትንሽ ተናግሬ ነበር ህይወቴን ስለቀየረ ቀላል መሳሪ ነበር ከዛ በፊት በጭራሽ ከቤቴ ርቄ አላውቅም ነበር ማላዊ ውስጥ ኮምፒውተር በጭራሽ ተጠቀሜ አላውቅም ድህረ ገጽ በጭራሽ ተመልክቼ አላውቅም በእለቱ መድረኩ ላይ በጣም ፈርቼ ነበር እንግሊዘኛ ጠፍቶብ ነበር ማስመለስ ፈልጌ ነበር (ሳቅ) እንደዚህ ያህል የበዙ አዙንጉዎች ተከብቤ አላውቅም ነጮች (ሳቅ) በጊዜው መናግር ያልቻልኩት ታሪክ ነበር ግን አሁን ጥሩ ስሜት ላይ ስለሆንኩ ያንን ታሪክ ዛሬ ላጋራቹ እፈልጋለሁ ቤት ውስጥ ሰባት ልጆች ነበርን ከኔ በስተቀር ሁሉም ሴቶች ናቸው ይሄ እኔ ነኝ ትንሽ ልጅ እያለሁ ከአባቴ ጋር የሳይንስን እውቀት ከማግኘቴ በፊት ተራ አርሶ አደር ነበርኩ ደሀ አርሷደሮች ባሉበት አገር ልክ እንደሌላው ሁሉ በቆሎ ነበር የምናበቅለው አንድ አመት ላይ እድላችን መጥፎ ሆኖ ነበር በ2001 በጣም ዘግናኝ ረሀብ አጋጠመን በአምስት ወር ውስጥ መላው ማላዊ እስኪ ሞት ተርቦ ነበር ቤተሰቤ በቀን አንዴ ነበር የሚመገበው ማታ ላይ ለእያንዳንዳችን ሶስት ጉርሻ ኒሲማ ይደርሰን ነበር ምግቡ ሰውነታችን ውስጥ ገብቶ ምንም አልጠቀመንም በማላዊ ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መክፈል ይጠበቅብናል በረሀቡ ምክያንት ትምህረቴን ለማቋረጥ ተገደድኩ አባቴን ስመለከት የደረቀውን ማሳ ሳይ ልቀበለው የምችለው የወደፊት እጣ አልነበረም ትምህርት ቤት መገኘት ያስደስተኝ ነበር ስለዚህ የሚቻለውን ለማድረግ ቆርጬ ነበር ትምህርት ለማግኘት ስለዚህ ወደ ቤተመጽሀፍት ሄድኩ መጽሀፍቶች አነበብኩ የሳይንስ መጻህፍት በተለይ የፊዚክስ እንግሊዘኛ ያን ያህል ማንበብ አልችልም ነበር የምስል ገለጻዎችንና ፎቶዎችን እጠቀም ነበር በነሱ ዙሪያ ያሉ ቃላት ለመረዳት አንድ መጽሀፍ እውቀትን በእጄ አስጨበጠኝ የንፋስ ተርባይን ውሀ ማፍለቅና ኤሌክተሪክ ማመንጨት ይችላል ይላል ውሀ ማፍለቅ መስኖ ማለት ነው ረሀብን መቋቋሚ ዘዴ በጊዜው ያ ነበር የኛ ችግር ስለዚህ ለራሴ አንድ የንፋስ ተርባይን ለመስራት ወሰንኩ ግን መስሪያ ቁሳቁሶች አልነበረኝም ስለዚህ ቁሻሻ መጣያ ቦታ ሄድኩ ቁሳቁሶችን ከዛ አገኘው ብዙ ሰዎች እናቴን ጨምሮ አብደሀል ሲሉኝ ነበር (ሳቅ) የትራክተር ንፋስ መስጫ፣ ንዘረት ተከላካይ፣ የፒቪሲ ቱቦ አገኘሁ የባይስክል ቸርኬና ያረጀ የባይስክል ዳይናሞ በመጠቀም መሳሪያዬን ገነባሁ መጀመሪያ ለአንድ መብራት ቀጥሎ አራት መብራቶች አራት መብራቶች ከነ ማብሪያ ማጥፊያ ሀይል ማገጃ ሳይቀር ከኤሌክትሪክ ደወል ጋር የሚመሳሰል ሌላኛው መሳሪያ ውሀ ያፈልቃል ለመስኖ የሚሆን የተወሰኑ ሰዎች ቤቴ ደጃፍ መሰለፍ ጀመሩ (ሳቅ) የሞባይል ስልካቸውን ሀይል ለመሙላት (ጭብጨባ) ላባርራቸው አልቻልኩም! (ሳቅ) ቀጥሎ ሪፖርተሮች መጡ ቀጥሎ ጦማሪያን ቀጥሎ ቴድ ከሚባል ነገር የስልክ ጥሪ መጣ በጭራሽ አውሮብላን አይቼ አላውቅም ነበር ሆቴል ውስጥ በጭራሽ አድሬ አላውቅም የዛን ቀን በአሩሻ መድረኩ ላይ እንግሊዘኛ ጠፋኝ እንደዚህ የመሰለ ነገር ነበር ያልኩት "ሞከርኩ እናም ተሳካልኝ" አንድ ነገር ማለት እፈልጋለሁ በውጭ ላሉ እኔን ለሚመስሉ ሁሉ ለአፍሪካኖች እና ለድሆች ህልማችሁን ለማሳካት ትግል ላይ ላላቹ አምላክ ይባርካቹ! ምናልባት አንድ ቀን በድህረ ገጽ ይሄን ታዩ ይሆናል እምላችሁ በራሳችሁ ተማመኑ እናም እመኑ ምንም ነገር ቢከሰት ተስፋ እንዳትቆርጡ አመሰግናለሁ! (ጭብጨባ)
Thank you. Two years ago, I stood on the TED stage in Arusha, Tanzania. I spoke very briefly about one of my proudest creations. It was a simple machine that changed my life. Before that time, I had never been away from my home in Malawi. I had never used a computer. I had never seen an Internet. On the stage that day, I was so nervous. My English lost, I wanted to vomit. (Laughter) I had never been surrounded by so many azungu, white people. (Laughter) There was a story I wouldn't tell you then. But well, I'm feeling good right now. I would like to share that story today. We have seven children in my family. All sisters, excepting me. This is me with my dad when I was a little boy. Before I discovered the wonders of science, I was just a simple farmer in a country of poor farmers. Like everyone else, we grew maize. One year our fortune turned very bad. In 2001 we experienced an awful famine. Within five months all Malawians began to starve to death. My family ate one meal per day, at night. Only three swallows of nsima for each one of us. The food passes through our bodies. We drop down to nothing. In Malawi, the secondary school, you have to pay school fees. Because of the hunger, I was forced to drop out of school. I looked at my father and looked at those dry fields. It was the future I couldn't accept. I felt very happy to be at the secondary school, so I was determined to do anything possible to receive education. So I went to a library. I read books, science books, especially physics. I couldn't read English that well. I used diagrams and pictures to learn the words around them. Another book put that knowledge in my hands. It said a windmill could pump water and generate electricity. Pump water meant irrigation, a defense against hunger, which we were experiencing by that time. So I decided I would build one windmill for myself. But I didn't have materials to use, so I went to a scrap yard where I found my materials. Many people, including my mother, said I was crazy. (Laughter) I found a tractor fan, shock absorber, PVC pipes. Using a bicycle frame and an old bicycle dynamo, I built my machine. It was one light at first. And then four lights, with switches, and even a circuit breaker, modeled after an electric bell. Another machine pumps water for irrigation. Queues of people start lining up at my house (Laughter) to charge their mobile phone. (Applause) I could not get rid of them. (Laughter) And the reporters came too, which lead to bloggers and which lead to a call from something called TED. I had never seen an airplane before. I had never slept in a hotel. So, on stage that day in Arusha, my English lost, I said something like, "I tried. And I made it." So I would like to say something to all the people out there like me to the Africans, and the poor who are struggling with your dreams. God bless. Maybe one day you will watch this on the Internet. I say to you, trust yourself and believe. Whatever happens, don't give up. Thank you. (Applause)