አንድ ነገር ላካፍለችሁ እፈልጋለሁ አዲስ አይነት የከፍተኛ ትምህርት አሰጣጥ መስፋት ከቻለ በአንድ ጊዜ የጋራ እውቀት በማዳበር ሚሊወኖች የፈጠራ ሰዎች እንዲበረታቱ የሚያደርግ ካልሰራንበት ግን ወደ ኋላ የሚያስቀር አለማችንን ተመልከቷ አንድ ቦታ ውሰዱና ትኩረት አድርጉበት የከፍተኛ የትምህርት እድል ፈላጊዎች ታገኛላቹ እስኪ የተወሰኑትን እንመልከት ፓትሪክ ፓትሪክ የተወለደው በላይቤሪያ ነው 20 ልጆች ባሉበት ቤተሰብ ውስጥ በእርስበርስ ጦርነቱ ወቅት እሱና ቤተሰቦቹ ወደ ናይጀሪያ ለመሰደድ ተገደው ነበር የነበረበት አስቸጋሪ ሁኔታ እንዳለ ሆኖ የሁለተኛ ደረጀ ትምህርቱን በከፍተኛ ውጤት ማጠናቀቅ ችሏል ከፍተኛ ትምህርት መቀጠል ይፈልግ ነበር ነገር ግን በቤተሰቦቹ ባሉበት የድህነት ህይወት ምክንያት ብዙም ሳይቆይ ወደ ደቡብ አፍሪካ እንዲሄድ ተደረገ ስራ ሰርቶ ገንዘብ ወደ ቤት በመላክ ቤተሰቦቹን እንዲመግባቸው ነበር ፓትሪክ ከፍተኛ ትምህርት ለመማር ያለውን ህልም አልተወም ነበር አንድ ቀን ማታ ከስራ መልስ መማር የሚቻልበትን አማራጭ ለማየት ድረ ገጽ ማሰስ ያዘ ዲቤን ተዋወቋት ዲቤ ፍሎሪዳ ነው የምትኖረው ቤተሰቦቹ የኮሌጅ ትምህርት አልተማሩም ዘመዶቿም ቢሆኑ ዲቤ ህይወቷን በሙሉ በስራ ነው ያሳለፈችው ግብር እየከፈለች፣ ከወር እስከ ወር እራስዋን ታስተዳድራለች በአሜሪካዊነት ህልም ኩራት እየተሰማት መቼም ሊሟላ የማይችል ህልም ነበር የከፍተኛ ትምህርት እስልተማረች ድረስ ነገር ግን ዲቤ ተቀማጭ ገንዘብ የላትም ለከፍተኛ ትምህርት የሚሆን ከፍላ ለመማር አትችልም ስራዋንም ማቋረት አትችልም ዌልን ተመለከቱት ዌል በሶርያ ነው ሚኖረው ከመነሻው አንስቶ የተለማመደው ስቃይን፣ ፍርሀትን እና ውድቀትን.. በሀገሩ ላይ የወረደውን ችግር ነበር በትምህርት ያምናል ይረዳ የነበረው እድሉን ማግኘት ከፍተኛ ትምህርት ለመማር ማለት የወደፊት እጣፈንታውን ለመኖርም ህልውናውን የሚቀይር እንደሚሆን ነበር ችግር በበዛበት በሱ አለም የከፍተኛ ትምህርት ለፓትሪክ፣ ለዲቤና ለዌል አልተቻላቸወም በተመሳሳይ ሁኔታ በሚሊየን ለሚቆጠሩ ችሎታው ያላቸውን ተማሪዎች በሚሊየን ለሚቆጠሩ የሁለተኛ ደረጃ ያጠናቀቁ ሚለየኖችን ለከፍተኛ ትምህርት ብቃቱ ላላቸው መማር ለሚፈልጉ ሚለየኖች ነገር ግን በተለያየ ምክንያቶች የመማር እድል ሊያገኙ አልቻሉም የመጀመሪያው የገንዘብ ችግር ነው ሁላችም እንደምናውቀው የዩኒቨርሲቲ ትምህርት ውድ ነው በብዙ የአለማችን ክፍሎች ከፍተኛ ትምህርት የሚቀመስ አይደለም በተለይ የመካከለኛ ገቢ ላላቸውም ዜጎች ሞናልባትም ይህ ከሁሉም የባሰው ችግር ሳሆን አይቀርም ማህበረሰባችን የሚያጋጥመው የከፍተኛ ትምህርት የሁሉም መብት መሆኑ አብቅቷል እናም ጥቂቶች ብቻ የሚታደሉት ሆኖአል በሁለተኛው ባህል ነው ለከፍተኛ ትምህርት ብቃቱ ያላቸው ተማሪዎች መክፈል እየቻሉ፣ መማርም እየፈለጉ፣ አይማሩም ምክንያቱም የተገባ አይደለም ለሴቶች የሚሆን ቦታም አይደለም ስለሚባል ይህ የብዙ አፍሪካዊያን ሴቶች ታሪክ ነው ለምሳሌ የከፍተኛ ትምህርት የሚከለከሉበት ምክንያት የባህል ተድፅኖ መኖር ነው ሶስተኛው ምክንያት ደግሞ ዩኔስኮ እንደሚገልፀው በ2025 100 ሚሊየን ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት ይነፈጋሉ በቂ መቀመጫ ባለመኖሩ ምክንያት ብቻ አነሱን ለማካተትና የሚፈለገውን ውጤት ለማምጣት የመመደቢያ ፈተና ይፈተናሉ ያልፋሉም ያም ሆኖ የመማር እድሉ አያገኙም ምክንያቱም በቂ የመማሪያ ቦታ ስለሌለ እነዚህ ናቸው ምክንያቶቹ ዩኒቨርስቲ ኦፍ ዘ ፒኘልን መሰረትኩት አትራፊ ያልሆነ፣ ከከፍያ ነፃ የሆነ ዲግሪ የሚስጥ ዩኒቨርስቲ አማራጭ ለመስጠት ሌላ አማራጭ ለሌላቸው በጣም አዋጭ የሆነ አማራጭ በስፋት መተግበር የሚችል ፈንቅሎ ሊወጣ የሚችልና አማራጭ ነባሩን የትምህርት ሒደት የሚቀይር ለከፍተኛ ትምህርት በሮችን የሚከፍት ለሁሉም ብቃት ላላቸው ተማሪዎች ምን ያህል ገቢ ቢኖራቸው፣ በየትኛውም አካባቢ ቢኖሩ የማህበረስብ ጫና ቢኖርባቸውም ፓትሪክ፣ ዲቤና ዌል ሶስት ብቻ ምሳሌዎች ናቸው ከ1,700 ከተቀበልናቸው ተማሪዎች ከ143 ሀገራት እኛ (ጭብጨባ)- አመሰግናለሁ
I would like to share with you a new model of higher education, a model that, once expanded, can enhance the collective intelligence of millions of creative and motivated individuals that otherwise would be left behind. Look at the world. Pick a place and focus on it. You will find humans chasing higher education. Let's meet some of them. Patrick. Patrick was born in Liberia to a family of 20 children. During the civil war, he and his family were forced to flee to Nigeria. There, in spite of his situation, he graduated high school with nearly perfect grades. He wanted to continue to higher education, but due to his family living on the poverty line, he was soon sent to South Africa to work and send back money to feed his family. Patrick never gave up his dream of higher education. Late at night, after work, he surfed the net, looking for ways to study. Meet Debbie. Debbie is from Florida. Her parents didn't go to college, and neither did any of her siblings. Debbie has worked all her life, pays taxes, supports herself month to month, proud of the American dream, a dream that just won't be complete without higher education. But Debbie doesn't have the savings for higher education. She can't pay the tuition. Neither could she leave work. Meet Wael. Wael is from Syria. He's experiencing firsthand the misery, fear and failure imposed on his country. He's a big believer in education. He knew that if he could find an opportunity for higher education, an opportunity to get ahead of the rest, he has a better chance to survive in a world turned upside down. The higher education system failed Patrick, Debbie and Wael, exactly as it is failing millions of potential students -- millions that graduate high school, millions that are qualified for higher education, millions that want to study yet cannot access it for various reasons. First: financial. Universities are expensive; we all know it. In large parts of the world, higher education is unattainable for an average citizen. This is probably the biggest problem facing our society. Higher education stopped being a right for all and became a privilege for the few. Second: cultural. Students who are qualified for higher education can afford -- want to study -- cannot, because it is not decent, it is not a place for a woman. This is the story of countless women in Africa, for example, prevented from higher education because of cultural barriers. And here comes the third reason: UNESCO stated that in 2025, 100 million students will be deprived of higher education, simply because there will not be enough seats to accommodate them, to meet the demand. They will take a placement test, they will pass it, but they still won't have access, because there are no places available. These are the reasons I founded University of the People, a nonprofit, tuition-free, degree-granting university to give an alternative, to create an alternative, to those who have no other; an alternative that will be affordable and scalable, an alternative that will disrupt the current education system, and open the gates to higher education for every qualified student regardless of what they earn, where they live, or what society says about them. Patrick, Debbie and Wael are only three examples out of the 1,700 accepted students from 143 countries. (Applause) Thank you.
አዲስ ነበር መፍጠር አይጠበቅብንም አልሰራ ያለውን ነገር ነው ማየት የሚጠበቅብን በተጨማሪ አስደናቂውን የኢተርኔት አቅምን መጠቀም ትምህርት ለማግኘት ለመስራት የተነሳነው ተምሳሌት ሊሆን የሚችል ሁሉምን አይነት ወጪ ሙሉ በሙሉ ሊያሶግድ የሚችል የከፍተኛ ትምህርት ክፍያን የሰራነውም ይሔን ነው መጀመሪያ ብሎኬትና ስሚንቶ የወጭ ይጠይቃሉ ዩኒቨርሲቲዎች ወጭ ይጠይቃሉ በኢንተርኔት ትምህርት ግን ምንም አይጠይቅም በእነዚህ ወጭዎች ተማሪዎቻችን ላይ መጫን አያስፈልግም ምክንያቱም ወጪ የለብንም የአቅም ሁኔታም አያሳስበንም ምክንያቱም የመቀመጫ ወንበር ገደብ የለብንም በኢንተርኔት ትምህርት ማንም በክፍል ውስጥ በመግባት መቆም አይጠበቅበትም መፃህፍት ማግኘት ሌላው ችግር ነው የኛ ተማሪወች ግን መፅሀፍ መግዛት አይጠበቅባቸውም ክፍት በሆኑ የትምህርት መርጃዎች እንዲሁም በጎ በሆኑ ፕሮፌስሮቻችን በሚሰጡን መፃህፍቶች መስረት ነፃና በቀላሉ ይማራሉ ተማሪዎቻችን መጽሀፍ እንዲገዙ አይገደዱም ሁሉም መሳሪያወቻችን በነፃ ይገኛሉ ፕሮፌሰሮቻችንም ቢሆኑ በጣም ወድ ክፍያ የሚጠይቁ ለኛ ተማሪዎች በነፃ ይገኛሉ ከ3000 በላይ የሚሆኑት ፕሬዘዳንቱንና ምክትል ቻንስለሩን ጨምሮ ፕሮፌሰሮችና የትምህርት አማካሪዎች ከታላላቅ ዩኒቨርሲቲዎች ለምሳሌ ኒውዮርክ ዩኒቨረሲቲ ያል፣ ባርክሌይ እና ኦክስፎርድ ተማሪዎቻችን ሊረዱ ተቀላቅለዋል በመጨረሻም በእርስ በርስ መማማር እናምናለን ይህን እንደመማማሪያ ምሳሌ እንጠቀምበታልን በአለምያሉ ተማሪዎቻችን ለማበረታታት እርስበርስ እንዲገናኙና እንዲረዳዱ ጊዜአቸውንም እንዲቆጥቡ ፕሮፌስሮቻችን በክፍል ስራዎችም ላይ ይስራሉ አንተርኔት አለምን አንድ መንደር ካደረጋት ይህ የትምህርት አይነት የወደፊት የአመራር ጥበብን ይቀይራል እንዴት አንደምንስራ ተመልከቱ ሁለት የትምህርት ዘርፎችን ብቻ እንሰጣለን ቢዝነስ አስተዳደርና ከኮንምፒውተር ሳይንስ ሁለቱ ፕሮግራሞች በአለማችን እጅግ ተፈላጊ የሆኑ ሁለቱ ፕሮግራሞች የበለጠ ለተማሪዎቻችን ስራ ማስገኘት የሚችሉ ናቸው ተማሪዎቻችንን ስንቀበል በትንሽ ክፍል ውስጥ ይካተታሉ ከ20 እስከ 30 ተማሪዎች በግለሰብ ደረጃ ትኩረት እንዲሰጣቸው ያስችላል በተጨማሪም ለእያንዳንዱ የዘጠኝ ሳምንት ትምህርት አዲስ የትምህርት ጓደኛ ይተዋወቃሉ ሁሉም አዲስ ተማሪዎች ከሁሉም የአለም ክፍሎች የመጡ ይሆናሉ በየሳምንቱ ወደ ክፍል ሲገቡ የሳምንቱን የመማሪያ የገለጻ ጽሁፍ ያገኛሉ የሚነበቡ ስራዎች፣ የቤት ስራዎችንና የፅሁፍ ስራዎችን ያገኛሉ በተጨማሪም የመወያያ ጥያቄዎችን ይህ ደግሞ ዋና የመማማሪያ ስልት ነው በየሳምንቱ ሁሉም ተማሪዎች በመወያያ ጥያቄዎች መሳተፍ አለባቸው አስተያየት መስጠትም ይጠበቅባቸዋል በሌሎች ሰዎች ስራዎች ላይም በዚህ መንገድ የተማሪዎቻችን እውቀት እንገባለን የአመላካከት አድማሰቸውንም እናሳድግላቸዋለን በተለያዩ ባህሎች በየሳምንቱ መጨረሻ ተማሪዎች ፈተና ይፈተናሉ የቤት ስራዎችንም ያስረክባሉ በተማሪዎቻችንም እርስ በርስ ይገመገማሉ በአስተማሪው መሪነት ውጤት ይሰጣቸዋል ከዚያም ወደ ሚቀጥለው ሳምንት ያልፋሉ በትምህርቱ መጨረሻም አጠቃላይ ፈተና ይወስዳሉ ውጤት ይሰጣቸዋል ከዚያም ወደመቀጥለው ትምህርት ያልፈሉ የክፍተኛ ትምህርት በሮችን ከፍተናል ለማንኛውም ብቃት ላለው ተማሪ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ያጠናቀቁ ሁሉ በቂ የእንግሊዘኛ ችሎታና የኢንተርኔት አገልግሎት ያላቸው ከኛ ጋር መማር ይችላሉ የድምፅ አንጠቀምም፣ ቪዲዮ አንጠቀምም የብርዶባንድ ኢንተርኔትም የግድ አይደለም ማንኛውም ተማሪ በየትኛውም የአለማችን ክፍል ያለ በማንኛውም አይነት የኢንተርኔት አገልግሎት ከእኛ ጋር መማር ይችላል ከክፍያ ነፃ ነን እኛ ተማሪዎቻችንን እንዲሸፍኑ የምንጠይቀው የሚፈተኑበትን የፈተና ወጪ ነው በአንድ ፈተና 100 ዳላር የሙሉ ጊዜ ባችለር ዲግሪ ተማሪ 40 ትምህርቶችን የሚወስድ በአመት የሚከፈለው 1000 ዳላር ነው 4,000 ዳላር ለሙሉ ዲግሪ ይህንን እንኳ መክፈል ለማይችሉ የተለያዩ አይነት ስኮላርሽፕ እንስጣለን አለማችን ማንም ከትምህርት እንዳይቀር ነው በገንዘብ እጥረት ምክንያት በ2016 ከሚኖሩን 5,000 ተማሪዎች ይህ መንገድ በገንዘብ አዋጭ ነው ከአምስት አመት በፊት ይሄ ህልም ብቻ ነበር በአሁን ሰአት ግን እውነታ ነው፡፡ በአለፈው ወር በትምህርት አሰጣጣችን ከፍተኛ ድጋፍ አግኝተናል ዮኒቨርሲቲ ኦፍ ዘ ፒፕል አሁን እውቅና አግኘቶል (ጭብጨባ) አመሰግናለሁ
(Applause) We didn't need to reinvent the wheel. We just looked at what wasn't working and used the amazing power of the Internet to get around it. We set out to build a model that will cut down almost entirely the cost of higher education. And that's how we did it. First, bricks and mortar cost money. Universities have expenses that virtual universities don't. We don't need to pass these expenses on to our students. They don't exist. We also don't need to worry about capacity. There are no limits of seats in virtual university. Actually, nobody needs to stand at the back of the lecture hall. Textbooks are also something our students don't need to buy. By using open educational resources and the generosity of professors who are putting their material up free and accessible, we don't need to send our students to buy textbooks. All of our materials come free. Even professors, the most expensive line in any university balance sheet, come free to our students. Over 3,000 of them, including presidents, vice chancellors, professors and academic advisers from top universities such as NYU, Yale, Berkeley and Oxford, came on board to help our students. Finally, is our belief in peer-to-peer learning. We use this sound pedagogical model to encourage our students from all over the world to interact and study together, and also to reduce the time our professors need to labor over class assignments. If the Internet has made us a global village, this model can develop its future leadership. Look how we do it. We only offer two programs: business administration and computer science, the two programs most in demand worldwide, the two programs that are likeliest to help our students find a job. When our students are accepted, they are placed in a small classroom of 20 to 30 students, to ensure that those who need personalized attention get it. Moreover, for every nine-week course, they meet a new peer, a whole new set of students from all over the world. Every week, when they go into the classroom, they find the lecture notes of the week, the reading assignment, the homework assignment, and the discussion question, which is the core of our studies. Every week, every student must contribute to the class discussion, and also must comment on the contribution of others. This way, we open our students' minds, we develop a positive shift in attitude toward different cultures. By the end of each week, the students take a quiz, hand in their homework, which are assessed by their peers under the supervision of the instructors, get a grade, move to the next week. By the end of the course, they take the final exam, get a grade, and follow to the next course. We open the gates for higher education for every qualified student. Every student with a high school diploma, sufficient English and Internet connection can study with us. We don't use audio, we don't use video. Broadband is not necessary. Any student from any part of the world with any Internet connection can study with us. We are tuition free. All we ask our students to cover is the cost of their exams, 100 dollars per exam. A full-time bachelor's degree student taking 40 courses will pay 1,000 dollars a year, 4,000 dollars for the entire degree. And for those who cannot afford even this, we offer them a variety of scholarships. It is our mission that nobody will be left behind for financial reasons. With 5,000 students in 2016, this model is financially sustainable. Five years ago, it was a vision. Today, it is a reality. Last month, we got the ultimate academic endorsement to our model. University of the People is now fully accredited. (Applause) Thank you.
ይህንን እውቅና ይዘን አሁን በስፋት ልናሳድገው ጊዜው ደርሷል የኛ አሰራር ተግባራዊ መሆን እንደሚችል አሳይተናል ሌሎች ዮኒቨርሲቲዎችን እንዲሁም የታደጊ ሀገራት መንግስታትን ይህን አሰራር እንዲያባዙት ጋብዘናል የከፍተኛ ትምህርት በሮቸን በሰፊው ለመክፈት አዲስ ዘመን እየመጣ ነው ዘመኑም ምስክር ይሆናል ለከፍተኛ ትምህርተ መስፋፋት እንቅፋት የሆነው አሁን የምናቀው አሰራር ተቀይሮ ለጥቂቶች የተገባ መሆኑ ቀርቶ ለሁሉም መሰረታዊ መብት ይሆናል በአቅም የሚቻልና ለሁሉም ተደራሽ ይሆናል አመሰግናለሁ (ጭብጨባ)
(Applause) With this accreditation, it's our time now to scale up. We have demonstrated that our model works. I invite universities and, even more important, developing countries' governments, to replicate this model to ensure that the gates of higher education will open widely. A new era is coming -- an era that will witness the disruption of the higher education model as we know it today, from being a privilege for the few to becoming a basic right, affordable and accessible for all. Thank you. (Applause)