ኬንያ ውስጥ ነው የምኖረው ከናይሮቢ ብሄራዊ ፓርክ አጠገብ በደቡብ በኩል ከበስተጀርባ ያሉት የአባቴ ላሞች ናቸው ከላሞቹ በስተጀርባ... ይሄ የናይሮቢ ብሄራዊ ፓርክ ነው የናይሮቢ ብሄራዊ ፓርክ በደቡብ በኩል አጥር የለውም ያ ማለት ልክ እንደ የሜዳ አህያ ያሉ እስስሳቶች ከፓርኩ በነጻነት ወጥተው ይመላለሳሉ ስለዚህ እንደ አንበሳ ያሉ አዳኝ እንስሳቶች ይከተሏቸዋል እናም እንደዚህ ነው የሚያደርጉት ከብቶቻችንን ይገድሉብናል! ማታ ላይ ከተገደሉት ላሞች መካከል ይቺ አንዷ ናት በጠዋት ስነሳ ሞቶ አገኘሁት መጥፎ ስሜት ነበር የተሰማኝ! ምክንያቱም ያለን ብቸኛ በሬ እሱ ነበር! በማህበረሰባችን በማሳይዎች ዘንድ የሚታመን ነገር አለ ከእንስሳቶቻችን ከመሬቱ ጋር ነው ከገነት የወረድነው እነሱን ለማገድ ነው! ለዛም ነው ከፍ ያለ ስፍራ የምንሰጣቸው! አንበሶቹን እየጠላሁ ነበር ያደግኩት ሞራንኖች ጦረኞች ናቸው! ማህበረሰባችንንና ከብቶቻችንን የሚጠብቁ እነሱ ናቸው ይሄ ችግር እነሱንም አበሳጭቷቸው ነበር ስለሆነ አንበሶችን ገደሏቸው! ይሄ ከተገደሉት ስድስት አንበሶች አንዱ ነው ለዛም ይመስለኛል በናይሮቢ ብሄራዊ ፓርክ የአንበሶች ቁጥር ያነሰው በማህበረሰባችን ከ6 እስከ 9 አመት የሆነ ልጅ የቤተሰቡን ከብቶች የመጠበቅ ሀላፊነት አለበት የኔም ስራ ይሄው ነበር! ችግሩን መቅረፊያ መንገድ መፈለግ ነበረብኝ መጀመሪያ የታየኝ ሀሳብ እሳት መጠቀም ነበር ምክንያቱም ሳስበው አንበሶቹ እሳት ይፈራሉ ግን ቆይቶ ስገነዘብ አዋጪ አልነበረም ለምን? ጭራሽ! አንበሶቹ... ከአጥሩ አልፈው እንዲያዩ ያግዛቸዋል ግን ተስፋ አልቆረጥኩም ጥረት ማድረግ ቀጠልኩ! ሁለተኛ የመጣልኝ ሀሳብ... ማስፈራሪያ ማቆም ነበር አንበሶቹን ለመሸወድ ነበር ጥረቴ ከከብቶቹ አጥር አጠገብ የቆምኩ እንዲመስላቸው ግን አንበሶቹ ብልጥ ነበሩ! (ሳቅ) በመጀመሪያው ቀን ማስፈራሪያውን አይተው ተመለሱ በሁለተኛው ቀን መተው... "ይሄ ነገር አይንቀሳቀስም ሁሌ እንደቆመነው" ይባባላሉ (ሳቅ) ስለዚህ ይዘሉና ከብቶቹን ይድላሉ አንድ ምሽት ላይ በከብቶቹ አጥር ዙሪያ ባትሪ ይዤ እየተራመድኩ ነበር በእለቱ አንበሶቹ ሳይመጡ ቀሩ እናም አንበሶች የሚንቀሳቀስ ብርሀን እንደሚፈሩ ተገለጸልኝ እንድ ሀሳብ መጣልኝ! ከልጅነቴ ጀምሮ... ቀኑን ሙሉ ክፍሌ ውስጥ ሆኜ እሰራ ነበር ከእናቴ አዲስ ሬድዮ ላይ ሳይቀር እቃ እወስድ ነበር! ያን ቀን ልትገለኝ ነበር! ግን ያው ስለ ኤሌክትሮኒክስ ብዙ ነገር ተማርኩ (ሳቅ) ያረጀ የመኪና ባትሪ አገኘው ጠቋሚ ሳጥን፣ ሞተር ሳይክል ላይ የሚገኝ ትንሽ መሳሪያ ነው ሞተር ነጂው ወደ ቀኝና ወደ ግራ መታጠፍ ሲፈልግ የሚረዳው ነው ብልጭ ድርግም ይላል ሌላ ማብሪና ማጥፊያ ነበረኝ ይሀ ደግሞ ከተሰበረ የእጅ ባትሪ የተገኘ ትንሽ አንፖል ነው ስለዚህ ሁሉን ነገር አስተካከልኩ እንደምታዩት የጸሀይ ብርሀን መሰብሰቢያው ባትሪውን ሀይል ይሞላዋል ባትሪው ደግሞ ለሳጥኗ ሀይል ይሰጣል ትራንስፎርመር ብዬ ነው ምጠራው ጠቋሚዋ ሳጥን ደግሞ መብራቱ ብልጭ ድርግም እንዲል ያደርጋል እንደምታዩት አንፖሎቹ ወደ ውጪ ነው የተሰቀሉት ምክንቱም አንበሶቹ በዛ በኩል ነው የሚመጡት በምሽት አንበሶቹ ሲመጡ የሚታያቸው እንደዚህ ነው መብራቱ ብልጭ ድርግም እያለ ይሸውዳቸዋል አንበሶቹ የሚያስቡት በላሞቹ አጥር ዙሪያ እየተራመድኩ እንደሆነ ነው እኔ ግን አልጋዬ ላይ ተኝቻለሁ! (ሳቅ) (ጭብጨባ) አመሰግናለሁ ይሄን የሰራሁት ከሁለት አመት በፊት ነበር ከዛን ጊዜ አንስቶ ከአንበሶቹ ጥቃት ደርሶብን አያውቅም ጎረቤቶቼ ስለ ሀሳቡ ሰምተው ነበር አንዷ አያታችን ነበረች አንበሶቹ ብዙ ከብቶች ገለውባት ነበር መብራቶቹን እንድ ገጥምላት ጠየቀችን እሺ አልኳት መብራቱን ሰቀልኩላት! እነዛ ከጀርባ የምታዩት የአንበሶቹ ብራት ነው እስካሁን ድረስ በአካባቢዬ ላሉ ሰባት ቤቶች ሰርቼላቸዋለሁ እናም በደንብ እየሰሩ ነው አሁን በመላው ኬንያ ሀሳቤን እየተጠቀሙበት ነው ሌሎችንም እንደ ጅብ አቦሸማኔ ለመሰሉ አውሬዎች ማስፈራሪያነት እየዋለ ነው በተጨማሪ ዝሆኖችን ከእርሻ ለማራቅ እየተጠቀሙበት ነው በዚህ ፈጠራ ምክንያት ነጻ የትምህርት እድል ለማግኘት ችያለሁ በኬንያ ምርጥ ከሚባሉት ትምህርት ቤቶች አንዱ ብሩክሀውስ አለማቀፍ ትምህርት ቤት በዚህ በጣም ከፍተኛ ጉጉት አድሮብኛል በአዲሱ ትምህርት ቤቴ በኩል እርዳታ እያደረጉ ነው ገቢ በማሰባሰብና ግንዛቤ በመፍጠር ጓደኞቼን ሳይቀር ወደ ቤት ይዣቸው መጣሁ በየቤቱ መብራቱን እየተከልን ነው እንዴት እንደሚሰራ እያስተማርኳቸው ነው እንግዲህ ከአመት በፊት በሳቫና ግራስ ላንድ የሚኖር ተራ ልጅ ነበርኩ የአባቴን ላሞች እያገድኩ ያኔ አውሮፕላን ሲያልፍ አይነበር እናም ለራሴ አንድ ነገር እል ነበር አንድ ቀን ውስጡ ገባለሁ ይሄው ዛሬ ለመጀመሪ ጊዜ ወደ ቴድ በአውሮፕላን መጣሁ አሁን ትልቁ ህልሜ ሳድግ የበረራ ኢንጅነርና ፓይለት መሆን ነው አንበሶቹን እጠላቸው ነበር ግን አሁን በፈጠራዬ ሰበብ የአባቶቼ ላሞችና አንበሶቹን ማትረፍ ችያለሁ ያለምንም ችግር ከአንበሶቹ ጋር መኖር ችለናል አሼዎ ኦሌኦን! በቋንቋዬ አመሰግናለሁ ማለት ነው (ጭብጨባ) "ምን ያህል አስደናቂ እንደሆነብን አታውቀውም ያንተን መሰል ታሪክ መስማት'' ክሪስ አንደርሰን የትምህርት እድል አገኘሀ? ታዲያ! ሌላ የኤሌክተሪካል ፈጠራዎች እየሰራህ ነው ቀጣይ ነገር ምንድነው? ቀጣዩ ፈጠራዬ የኤሌክትሪክ አጥር መስራት ነው የኤሌክትሪክ አጥር? የኤሌክትሪክ አጥር እንደ ተፈጠረ አውቃለሁ የራሴን የተለየ መፍጠር ነው ምፈልገው (ሳቅ) እስካሁን መቼም አንዴ ሞክረኀል አይደል! በፊት ሞክሬ ነበር ግን ስለነዘረኝ ተውኩት (ሳቅ) ሪቻርድ ቱሬሬ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የተገኘህ ምርጥ ነገር ነህ በያንዳንዱ እርምጃህ ጎንህ ሆነን እናበረታታሀለን ጎደኛዬ በጣም አመሰግናለሁ! አመሰግናለሁ (ጭብጨባ)
This is where I live. I live in Kenya, at the south parts of the Nairobi National Park. Those are my dad's cows at the back, and behind the cows, that's the Nairobi National Park. Nairobi National Park is not fenced in the south widely, which means wild animals like zebras migrate out of the park freely. So predators like lions follow them, and this is what they do. They kill our livestock. This is one of the cows which was killed at night, and I just woke up in the morning and I found it dead, and I felt so bad, because it was the only bull we had. My community, the Maasai, we believe that we came from heaven with all our animals and all the land for herding them, and that's why we value them so much. So I grew up hating lions so much. The morans are the warriors who protect our community and the livestock, and they're also upset about this problem. So they kill the lions. It's one of the six lions which were killed in Nairobi. And I think this is why the Nairobi National Park lions are few. So a boy, from six to nine years old, in my community is responsible for his dad's cows, and that's the same thing which happened to me. So I had to find a way of solving this problem. And the first idea I got was to use fire, because I thought lions were scared of fire. But I came to realize that that didn't really help, because it was even helping the lions to see through the cowshed. So I didn't give up. I continued. And a second idea I got was to use a scarecrow. I was trying to trick the lions [into thinking] that I was standing near the cowshed. But lions are very clever. (Laughter) They will come the first day and they see the scarecrow, and they go back, but the second day, they'll come and they say, this thing is not moving here, it's always here. (Laughter) So he jumps in and kills the animals. So one night, I was walking around the cowshed with a torch, and that day, the lions didn't come. And I discovered that lions are afraid of a moving light. So I had an idea. Since I was a small boy, I used to work in my room for the whole day, and I even took apart my mom's new radio, and that day she almost killed me, but I learned a lot about electronics. (Laughter) So I got an old car battery, an indicator box. It's a small device found in a motorcycle, and it helps motorists when they want to turn right or left. It blinks. And I got a switch where I can switch on the lights, on and off. And that's a small torch from a broken flashlight. So I set up everything. As you can see, the solar panel charges the battery, and the battery supplies the power to the small indicator box. I call it a transformer. And the indicator box makes the lights flash. As you can see, the bulbs face outside, because that's where the lions come from. And that's how it looks to lions when they come at night. The lights flash and trick the lions into thinking I was walking around the cowshed, but I was sleeping in my bed. (Laughter) (Applause) Thanks. So I set it up in my home two years ago, and since then, we have never experienced any problem with lions. And my neighboring homes heard about this idea. One of them was this grandmother. She had a lot of her animals being killed by lions, and she asked me if I could put the lights for her. And I said, "Yes." So I put the lights. You can see at the back, those are the lion lights. Since now, I've set up seven homes around my community, and they're really working. And my idea is also being used now all over Kenya for scaring other predators like hyenas, leopards, and it's also being used to scare elephants away from people's farms. Because of this invention, I was lucky to get a scholarship in one of the best schools in Kenya, Brookhouse International School, and I'm really excited about this. My new school now is coming in and helping by fundraising and creating an awareness. I even took my friends back to my community, and we're installing the lights to the homes which don't have [any], and I'm teaching them how to put them. So one year ago, I was just a boy in the savanna grassland herding my father's cows, and I used to see planes flying over, and I told myself that one day, I'll be there inside. And here I am today. I got a chance to come by plane for my first time for TED. So my big dream is to become an aircraft engineer and pilot when I grow up. I used to hate lions, but now because my invention is saving my father's cows and the lions, we are able to stay with the lions without any conflict. Ashê olên. It means in my language, thank you very much. (Applause) Chris Anderson: You have no idea how exciting it is to hear a story like yours. So you got this scholarship.Richard Turere: Yep. CA: You're working on other electrical inventions. What's the next one on your list? RT: My next invention is, I want to make an electric fence.CA: Electric fence? RT: But I know electric fences are already invented, but I want to make mine. (Laughter) CA: You already tried it once, right, and you --RT: I tried it before, but I stopped because it gave me a shock. (Laughter) CA: In the trenches. Richard Turere, you are something else. We're going to cheer you on every step of the way, my friend. Thank you so much.RT: Thank you. (Applause)