በአሜሪካ የትኛውም መንገድ ላይ ቆማችሁ ራሳችሁን አስቡት እና ጃፓናዊ ሰውዬ መጥቶ እንዲ ቢላቹ ‹ይቅርታ! ይሄ ብሎክ ምን ይባላል› እርሶ ሲመልሱ ‹ይሄ! ኦክ መንገድ ይባላል ያ ደሞ ኤልም መንገድ ይባላል ይሄ 26ኛ ያ ደሞ 27ኛ ነው› እሱም እሺ በማለት ‹እሺ! ያኛው ብሎክስ ምን ይባላል?› እርሶም ‹እንግዲ! ብሎኮች ስም የላቸውም፡፡ መንገዶች ናቸው ስም ያላቸው፤ ብሎኮች በመንገዶች መሀከል ስም አልባ የሆኑ ቦታዎች ናቸው› እሱም ትንሽ ግራ በመጋባት አዝኖ ይሄዳል አሁን ደሞ በጃፓን የትኛውም መንገድ ላይ ቆመው እንዳሉ ያስቡ ከጎን ወደላው ሰው ይዞራሉ እና ምን ይላሉ ይቅርታ! ይሄ መንገድ ምን ተብሎ ነው ሚጠራው? እነሱም ‹እንግዲ ያ ብሎክ 17፤ ይሄ ደሞ ብሎክ 16› እርሶም ‹እሺ ግን የመንገዱ ስም ምንድን ነው?› እነሱም ምን ብለው ይመልሳሉ ‹መንገዶች ስም የላቸውም ብሎኮች ስም አላቸው ጎግል ካርታ ላይ ይመልከቱ፡፡ ያሉት ብሎኮች 14፣ 15፣ 16፣ 17፣ 18፣ 19 እነዚ ብሎኮች በሙላ ስም አላቸው መንገዶች በብሎኮች መሀከል የሚገኙ ስም አልባ የሆኑ ቦታዎች ናቸው› እርሶም ምን ይላሉ ‹እሺ! የቤትዎን አድራሻ እንዴት ያውቃሉ?› እሱም ምን ይመልሳል ‹ቀላል ነው! ይሄ ቀጠና ስምንት፤ ያ! ብሎክ 17፤ የቤት ቁጥር አንድ› እርሶም ሲመልሱ ‹እሺ! በሰፈር ውስጥ ስንቀሳቀስ የቤት ቁጥሮቹ በተርታ ይደለም የተቀመጡት› እሱም ሲመልስ ‹በተርታ ይሄዳሉ፡፡ ተገንብተው ባለቁበት ጊዜ ነው የሚሰየሙት፡፡ በብሎክ ውስጥ መጀመሪያ የተገነባው ቤት ቁጥር አንድ ነው፡፡ ሁለተኛ የተገነባው የቤት ቁጥሩ ሁለት ነው ሶስተኛ የተገነባው ቁጥር ሶስት ነው፡፡ ቀላል እናም ግልፅ ነው፡፡ ስለዚ አንዳንዴ ደስ ይለኛል የዓለምን ተቃራኒ ቦታ መሄድ የራሳችን አመለካከት እንዳለን ለማወቅ እናም ከኛ ተቃራኒ አመለካከት እንዳለ ለመረዳት ለምሳሌ በቻይና ሐኪሞች አሉ ስራቸው የናንተን ጤና መጠበቅ እንደሆነ የሚያምኑ እናም ጤነኛ ሆነው ባሳለፉት ወራት ይከፍሏቸዋል ሲታመሙ ደሞ አይከፍሏቸውም ምክንያቱም ስራቸውን በአግባብ ስላልተወጡ ሀብታም የሚሆኑት እርስዎ ጤናኛ ሲሆኑ ነው እንጂ እርስዎ ሲታመሙ አይደለም (ጭብጨባ) በብዙ ሙዚቃ ውስጥ፤ ‹አንድን› እናስባለን የሙዚቃ አጀማመርን ስናይ አንድ ፣ ሁለት ፣ ሶስተ ፣ አራት ግን በምዕራብ አፍሪካ ሙዚቃ፤ ‹አንድ› የመጨረሻ እንደሆነ ነው ሚታሰበው ለልክ ከአረፍተ ነገር መጨረሻ አራት ነጥብ እንደሚገባው በሙዚቃው አሰራር ብቻ ሳይሆን የምትሰሙት፤ ሙዚቃውንም የሚጨርሱበት አካሄድ ነው ሁለት ፣ ሶስት ፣ አራት ፣ አንድ እና ይሄ ካርታ እራሱ ልክ ነው (ሳቅ) የሆነ አባባል አለ ስለህንድ የሚያነሱት ማንኛውም እውነታ ተቃራኒውም እውነት ነው ስለዚ እንዳንረሳ በቴድም ሆነ ሌላ ቦታ ማንኛውም ምርጥ ሀሳብ ቢያነሱም ወይም ቢሰሙም ተቃራኒውም እውነት ሊሆን ይችላል (ጃፓንኛ) በጣም ነው ማመሰግነው!
So, imagine you're standing on a street anywhere in America and a Japanese man comes up to you and says, "Excuse me, what is the name of this block?" And you say, "I'm sorry, well, this is Oak Street, that's Elm Street. This is 26th, that's 27th." He says, "OK, but what is the name of that block?" You say, "Well, blocks don't have names. Streets have names; blocks are just the unnamed spaces in between streets." He leaves, a little confused and disappointed. So, now imagine you're standing on a street, anywhere in Japan, you turn to a person next to you and say, "Excuse me, what is the name of this street?" They say, "Oh, well that's Block 17 and this is Block 16." And you say, "OK, but what is the name of this street?" And they say, "Well, streets don't have names. Blocks have names. Just look at Google Maps here. There's Block 14, 15, 16, 17, 18, 19. All of these blocks have names, and the streets are just the unnamed spaces in between the blocks. And you say then, "OK, then how do you know your home address?" He said, "Well, easy, this is District Eight. There's Block 17, house number one." You say, "OK, but walking around the neighborhood, I noticed that the house numbers don't go in order." He says, "Of course they do. They go in the order in which they were built. The first house ever built on a block is house number one. The second house ever built is house number two. Third is house number three. It's easy. It's obvious." So, I love that sometimes we need to go to the opposite side of the world to realize assumptions we didn't even know we had, and realize that the opposite of them may also be true. So, for example, there are doctors in China who believe that it's their job to keep you healthy. So, any month you are healthy you pay them, and when you're sick you don't have to pay them because they failed at their job. They get rich when you're healthy, not sick. (Applause) In most music, we think of the "one" as the downbeat, the beginning of the musical phrase: one, two, three, four. But in West African music, the "one" is thought of as the end of the phrase, like the period at the end of a sentence. So, you can hear it not just in the phrasing, but the way they count off their music: two, three, four, one. And this map is also accurate. (Laughter) There's a saying that whatever true thing you can say about India, the opposite is also true. So, let's never forget, whether at TED, or anywhere else, that whatever brilliant ideas you have or hear, that the opposite may also be true. Domo arigato gozaimashita.